ሁለተኛው የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል በቲክቶከሮች አሸናፊነት ተጠናቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

ለሁለተኛ ጊዜ በልዩ ድምቀት ሲካሄድ የቆየው የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል የቲክቶክ ቡድን ዋንጫውን በማንሳት በድል ተጠናቋል።

ከሚያዚያ 22 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ FBE ካምፓስ ስፖርት ሜዳ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ቲክቶከሮች፣ የስፖርት ጋዜጠኞች፣ ድምፃዊያን እና አርቲስቶች በምድብ ተከፋፍለው ተሳታፊ ሆነዋል።

በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩት ቲክቶከሮች እና የስፖርት ጋዜጠኞች ለፍፃሜው ጨዋታ መድረስ የቻሉ ሲሆን በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለቱም ቡድኖች አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የፍፁም ቅጣት ምት የቲክቶክ ባለሙያዎች ቡድን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ሻምፒዮና መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ለደረጃ በተካሄደ ጨዋታ ድምፃዊያን አርቲስቶችን በማሸነፍ የሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በውድድሩ ማጠቃለያ ላይ ለአሸናፊዎች የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ቲክቶከሮች የውድድሩ ሻምፒዮና በመሆን የወርቅ ሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችለዋል። ውድድሩን በሁለተኝነት ያጠናቀቁት የስፖርት ጋዜጠኞች የብር ሜዳልያ እንዲሁም ድምፃዊያን የነሐስ ሜዳልያ እና የፀባይ ዋንጫ (Fair Play) ተሸላሚ ሆነዋል።

የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ያኪ ከቲክቶከሮች ሆኗል

ኤቢ የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢና የውድድሩን ምርጥ ግብ በማስቆጠር ተሸልሟል

የድምፃውያን ቡድነወ ሶስተኛ ከመውጣት በተጨማሪ የፀባይ ዋንጫ ባለቤትም ሆነዋል

ይህ ተወዳጅነትን እያገኘ የመጣው የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል በየዓመቱ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2