በሃፒነስ ኬተሪንግ ልዩ የምሳ ግብዣና እውቅና ተቸረው
#Ethiopia | በቅርቡ በተካሄደ የቦክስ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ወጣት ስፖርተኞች መስፍን ቢሩ እና ኤርምያስ መስፍን ለቤተሰቦቻቸው ባሳዩት ጥልቅ ፍቅርና በላቀ ጨዋነታቸው የብዙዎችን አድናቆት አትርፈዋል።
ይህንን ተከትሎ በሆቴልና ኬተሪንግ ዘርፍ ስመ ጥር የሆነው ሃፒነስ ኬተሪንግ በበጎ አድራጎት ተቋሙ ሃፒነስ ኬር አማካኝነት ለሁለቱ ቦክሰኞች ልዩ እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
የእውቅና መርሃ ግብሩ ውድድሩ በተከናወነበት ስፍራ የተካሄደ ሲሆን ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባዘጋጀው የጋራ የምሳ ፕሮግራም ላይ ስነ ስርዓቱ በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።
በወቅቱም ስፖርተኞቹ ከውድድር ባለፈ ላሳዩት ማህበራዊ ጨዋነትና ለቤተሰቦቻቸው ላላቸው ታማኝነት የሚመጥን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የሃፒነስ ኬተሪንግ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ንጉሤ በዝግጅቱ ላይ እንደገለጹት አባታቸው አቶ ንጉሤ ወልደገብርኤል ዛሬ በህይወት ባይኖሩም የተከሉት የመልካም አስተዳደግና የጥበብ ዘር ለዛሬው ስኬታቸው መሰረት ሆኗል።
እነዚህ ወጣቶች ለአባቶቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው ያሳዩት ክብር ድርጅታቸው ከሚያከብረው የቤተሰብ እሴት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ በመሆኑ እውቅናው እንደተሰጣቸው አብራርተዋል።
ሃፒነስ ኬር የተመሰረተው መሰል የቤተሰብ እሴቶችን ለማጠናከርና በማህበረሰቡ ውስጥ በጎ ስነ ምግባር እንዲሰፍን ለማገዝ ነው።
ድርጅቱ በውድድሩ ስፍራ ተገኝቶ ሽልማቱን ማበርከቱ ወደፊት ትውልድ በሚገነቡና በቤተሰብ ዙሪያ በሚያጠነጥኑ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በቁርጠኝነት ለመሳተፍ ስላለው እቅድ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል።
ተቋሙ እንዲህ ያሉ ስፖርታዊ ጨዋነቶችንና ቤተሰብን መሰረት ያደረጉ ተግባራትን ደግፎ ለማስቀጠል ቃል ገብቷል።
#happinesscatering #boxingethiopia #familyvalues #sportmanship #charity #ethiopiansports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.