ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዜጎቿን በፈቃደኝነት ልታስወጣ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

በደቡብ አፍሪካ በውጭ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና የጥላቻ ንግግሮች እየተባባሱ መምጣታቸውን ተከትሎ፤የናይጄሪያ መንግስት ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎቿን በነጻ በረራ ለማስወጣት ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢአንካ ኦዱሜግው ኦጁኩ እንደገለጹት፤ እስካሁን 1መቶ30 ዜጎች ለመመለስ የተመዘገቡ ሲሆን ቁጥሩም ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በናይጄሪያውያን ላይ እየደረሰ ባለው ግድያ እና የንግድ ተቋማት ጥቃት ማዘናቸውን ገልጸው፤የደቡብ አፍሪካን ከፍተኛ ኮሚሽነር በመጥራት መንግስታቸው ያለውን ‹‹ጥልቅ ስጋት››በይፋ አሳውቀዋል።

በደቡብ አፍሪካ ባለፉት ሳምንታት በተቀሰቀሰው የጸረ-ስደተኞች እንቅስቃሴ አራት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ለሞትና ለንብረት ጥቃት ተዳርገዋል።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጥቃቱን ቢያወግዙም ጸረ-ስደተኛ ቡድኖች ግን ‹‹የውጭ ዜጎች ስራ ይነጥቁናል››በሚል ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል።

ሳራ ዮሐንስ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2