አዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያው ሊለማ ነውከ50 ዓመታት በላይ ብቸኛ የአገራችን ብሔራዊ ስታድየም በመሆን ሲያገለግል የቆየው አዲስ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያው ሊለማ ነው
ከ50 ዓመታት በላይ ብቸኛ የአገራችን ብሔራዊ ስታድየም በመሆን ሲያገለግል የቆየው አዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያው የአዲስ አበባ ከተማን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጡ አዳዲስ ገፅታዎችን በመጨመር በ2 ቢሊየን ብር ሊለማ ነው::
ልማቱ የሚያጠቃልላቸው:-
1ኛ :- በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በአፍሪካ ትልቅ የሆነው በአንድ ጊዜ ከ200 ሰዎች በላይ ማስተናገድ የሚችል የህዝብ መዋኛ ገንዳ::
2ኛ:- ከመስቀል አደባባይ ጋር በምድር ውስጥ (underground) የሚያገናኝ ከመስቀል አደባባይ ከፓርኪንግ ስታድየም ውስጥ ለውስጥ የሚያገናኝ መንገድ::
3ኛ:- የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስፓርት ሙዝየም በመገንባት ኢትዮጵያ ለዓለም እና ለአፍሪካ በስፓርት ዘርፍ ያበለፅገችው ጉልህ የአትሌቲክስና እግር ካስ ሌሎችንም የያዘ ታላቅ ሙዚየም, የስፓርት አልባሳትና ቁሳቁስ መሸጫ እና ጂምናዝየም::
ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዩችና መናፈሻዎችን በማካተት በ6 ወራት ለህዝብ ክፍት ለማድረግ ስራ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልፃል::
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2