ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ መከላከያ ክትባት የክሊኒካዊ ሙከራን በድል አጠናቀቀች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከናወን የቆየው የማርበርግ ቫይረስ መከላከያ ክትባት የክሊኒካዊ ፍተሻ በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የጥናቱ መጠናቀቅ ሳይንሳዊ ምርምርን ወደ ተግባር የመለወጥ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።

ክሊኒካዊ ፍተሻው በከባድ ፈተናዎች ውስጥም ውጤታማ ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ያሳየ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ወረርሽኙን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ያደረጉት የጋራ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ የመጀመሪያው ክሊኒካዊ ፍተሻ ኢትዮጵያ በምርምር ዘርፉ ላደረገችው ጥረት ውጤታማ ማሳያ ነው።

በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የተገነቡት ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ለማሳደግና ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ሚናቸው የጎላ መሆኑም ተመላክቷል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ምንም ዓይነት ክትባት ባልነበረበት ሁኔታ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በሽታው በታወቀ በ24 ቀናት ውስጥ የክትባት ሙከራው መጀመሩን አስታውሰዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፍተሻ ሂደቱን የሚያሳይ ገለጻ የቀረበ ሲሆን ለስኬቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።

#የጤናሚኒስቴር #የማርበርግቫይረስ #የክትባትምርምር #አርማወርሀንሰን #ጤና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2