የጉምሩክ ኮሚሽን ከሚያዚያ 11 እስከ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 386.2 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14.5 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 400.7 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ጅግጅጋ ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ እና ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 126 ሚሊዮን፣ 95 ሚሊዮን እና 44 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣በፌደራል ፖሊስ፣በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣በጥቆማ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 26 ተጠርጣሪዎች እና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን

Source: Yeneta Tube









No comments yet.