የብልጽግናን ፖስተር የቀደደው በ9 ወር እስራት ተቀጣ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | በአርባ ምንጭ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮችን በመቅደድ የወንጀል ድርጊት የፈጸመው ተከሳሽ ተመስገን ካርታ፣ በ9 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የአርባ ምንጭ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

​ተከሳሹ ተመስገን ካርታ ማክሰኞ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 12፡30 ገደማ፣ በሼቻ ክፍለ ከተማ “ባይራ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመብራት ፖል ላይ የተለጠፉ ሁለት የምርጫ ማስታወቂያዎችን በመቅደድ ወንጀል መፈጸሙ ተረጋግጧል። የተቀደዱት ፖስተሮች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለአርባ ምንጭ ምርጫ ክልል የቀረቡ የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የምርጫ ምልክት (የስንዴ ነዶ) ያለባቸው ነበሩ።

​ዓቃቤ ሕግ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 158ን መሠረት በማድረግ ክስ መስርቶበታል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ በ9 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: