#Ethiopia | የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሁሉንም የንግድ መገናኛ ብዙኃን ተቋማት ወደ አዲስ የዲጂታል አሠራር ለማሸጋገር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ይህንን ውጥን ከግብ ለማድረስም ፈቃድ ያላቸው የንግድ ብሮድካስት አገልግሎት ሰጪዎች የሚፈለጉባቸውን መረጃዎች እስከ ሚያዝያ 29 ቀን ድረስ አሟልተው እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
ባለሥልጣኑ ተቋማቱ እንዲያቀርቡ የጠየቃቸው ዝርዝር መረጃዎች የሥራ አስኪያጅ፣ የባለቤት፣ የዋና አዘጋጅ እና የፕሮግራም ኃላፊ ስሞችን የሚመለከቱ ናቸው።
በተጨማሪም የመገናኛ ብዙኃን ድርጅቶቹን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሪፖርት፣ የፋይናንስ ምንጭ ማስረጃ እንዲሁም ዓመታዊ የገቢና ወጪ መግለጫዎችን እንዲያቀርቡ አሳስቧል።
#የመገናኛብዙኃን #ዲጂታልአሠራር #ኢትዮጵያ #ዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #AddisAbabaProperty
Source: GetuTemesgen









No comments yet.