እርሱ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነውና ጸንተን እንለፍ

- Advertisement -
Sidebar AD

አማኑኤል በኩነት በተዋሕዶ የተሰጠው የሥግው ቃል ስም ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ “እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” በማለት በትንቢት እንደተናገረው የተስፋው ቃል ይፈጸም ዘንድ በዘመነ ሥጋዌ እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወለደ፤ ከእኛ ጋርም ሆነ፡፡ ሰዎች በሕይወት ዘመናችን ችግርና መከራ ሲጸናብንና ፈተናችን ሲበዛ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳልሆነ አንዳንዴም ጨርሶ እንደተወን እናስባለን፡፡ ሆኖም እርሱ ሁሌም ከእኛ ጋር ነውና፣ ሁሉንም በምክንያት ያደርጋልና ፈተናውን ለበጎ ነው በማለት ጸንተን መጓዝ ያስፈልጋል፡፡

በተለይም በዚህ ጊዜ ችግራችን በዝቶ፣ የእርሱ በርሱ ጦርነት ብሶ፣ የክርስቲያኖች ሞት እንደተራ ነገር ተቆጥሮ ተጠያቂ በጠፋበት ወቅት እኛ ክርስቲያኖች ስለደማችን የሚጮህልን በሌለበት፣ የልጆቹን ደም የሚመልስ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርገን በሃይማኖት ልንጸናና ልንበረታ ይገባል እንጂ ችግራችንን እያገዘፍን አምላካችንን የምናማርር ከሆነ መፍትሔ አናገኝም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍጥረቱን በሙሉ የማይረሳ አምላክ ስለሆነ ከሁላችንም ጋር ይኖራል፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው እርሱን በሚያስደስት ክርስቲያናዊ ሕይወት፣ በሕጉ ጸንተን፣ በመገዛትና ትእዛዛቱን በመፈጸም መኖር ነው፡፡

አማኑኤል ‹አማነ› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፤ ትርጓሜውም የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ደግሞ ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ የተዋሐደ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር እንደኛ የሆነ ማለት ነው። አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሞት ፍርድ በተፈረደበት ጊዜ አምላኩ እግዚአብሔር እዲያድነው ስለተማጸነው በርኅራኄው ወደ ቀድሞ ቦታው እንደሚመልሰው በሰጠው ተስፋ ከልጅ ልጁ ተወለዶ አዳነው፡፡ በዚያችም በተከበረች ቀን ትንቢቱ ተፍጽሞ አምላካችን ከእኛ ጋር ሆነ፡፡ ይህን ስም ተመክተው ነው ገዳማውያኑ ዓለምን ንቀው የመነኑት፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: