#Ethiopia | በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ስልጠና መስጠት የሚችሉት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተቋማት ብቻ መሆናቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ከአዲስ ኤፍኤም 97.1 ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በዘርፉ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል የብቃት ማረጋገጫ ሊኖረው ይገባል።
እስካሁን ባለው ሂደት ኢንስቲትዩቱ ለማንኛውም የግል ተቋምም ሆነ ግለሰብ የማሰልጠን ፈቃድ እንዳልሰጠ የገለጹት ዳይሬክተሩ ይህንን መመሪያ ተላልፎ የሚገኝ አካል በሕግ እንደሚጠየቅ አስገንዝበዋል።
ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መሰጠት እንደሚጀምርም ተጠቁሟል።
በአዋጅ ቁጥር 510/2014 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በዘርፉ ማህበረሰቡን የማሰልጠን እና ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ኃላፊነት የኢንስቲትዩቱ መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ፈቃድ በሌላቸው አካላት በሚደረጉ አደናጋሪ ስልጠናዎች እንዳይታለል እና አላስፈላጊ ወጪዎች እንዳይዳረግ ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም በዘርፉ መሰማራት የሚፈልግ አካል ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመቀናጀት እና የሀገሪቱን የኤአይ ፖሊሲና ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተመላክቷል።
በኃይለሚካኤል አበበ
#አርቴፊሻልኢንተለጀንስ #ቴክኖሎጂ #ትምህርት #ስልጠና #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.