በውጭ የሚኖሩ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ቁጥርን ከባንክ ሂሳብ ጋር ለማስተሳሰር‼️
የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር ጋር በማስተሳሰሩ ሂደት በውጭ ለሚኖሩ ዜጎች የማረጋገጫ ኮድ (OTP) በኢሜል የሚላክበት አሰራር መኖሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አሳውቋል።
የፕሮግራሙ የምዝገባ ኦፕሬሽን መሪ አቶ ሄኖክ ጥላሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ ዜጎች መረጃቸውን በኢሜል ጭምር በማስመዝገብ ከርቀት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ብዙዎች የሚጠይቁትን “ ከሀገር ውጭ ያለን ሰዎች የማረጋገጫ ኮድ (OTP) በስልካችን ካልመጣልን ምን እናድርግ ? ” የሚለውን ስጋት በተመለከተ አቶ ሄኖክ ሲመልሱ “ ኢሜል ያላችሁ ሰዎች በፋይዳ ምዝገባቸው ላይ ኢሜላቸውን አብረው እንዲያስመዘግቡ በጣም ነው የምናበረታታው፣ ስልክ ቁጥሩ በተለያየ ምክንያት ቢጠፋ ወይም በኔትወርክ ምክንያት መልዕክት ባይቀበል፣ የማረጋገጫ ኮዱ (OTP) ወዲያውኑ አብሮ ኢሜሉን ላስመዘገበ ሰው ወደ ኢሜሉ ይገባል ” ብለዋል።
እንደ ሃላፊው ገለጻ፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ ዜጎች በውጭ ሀገር ሆነው የኢሜል አማራጭን በመጠቀም የባንክ ሂሳባቸውንና የፋይዳ ቁጥራቸውን “ሀርሞናይዝ” እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ አገልግሎት እያንዳንዱ ባንክ ጋር በዲጂታል አማራጮች ስለተተገበረ፣ ተገልጋዮች በኢትዮጵያ ወሰን ውስጥ ብቻ ሳይሆኑ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው የባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልጋቸው መስተናገድ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ፋይዳ ተመዝግበው ኢሜል ያላስመዘገቡ ካሉም ” በፋይዳ የመረጃ ማሻሻያ ስርዓት ላይ መረጃ ማሻሻል እያደረጉ ኢሜላቸውን ቢያስገቡ ለሌላ ጊዜም ሲፈልጉት ይጠቅማቸዋል ” ብለዋል።
በውጭ ሀገር የሚኖሩና እስካሁን የፋይዳ መታወቂያ ያልወሰዱ ዜጎችን በተመለከተም ኦፕሬሽን መሪው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ሄኖክ በአሁኑ ወቅት የፋይዳ ምዝገባ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (አቡዳቢና ዱባይ) ብቻ የተጀመረ በመሆኑ፣ በሌሎች ሀገራት ያሉ ዜጎች ባንኮች በሚጠይቋቸው መረጃዎች መሰረት ከዚህ አስገዳጅ ትስስር ለጊዜው ነፃ (Exempt) ሊደረጉ የሚችሉበት አሰራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል።
“ ደንበኞቻቸው ውጭ ሀገር ነዋሪ ከሆኑና ሀገር ውስጥ የሌሉ መሆኑን የሚያስረዳ መረጃ ካቀረቡ፣ ከዚህ ትስስር ነፃ እንዲደረጉ ብሔራዊ ባንክ ለእያንዳንዱ ባንክ ሰርኩላር ልኳል ስለዚህ ውጭ ያሉ ሰዎች ስጋት እንዳይገባቸው ” ሲሉ አቶ ሄኖክ አረጋግጠዋል።
ሆኖም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ትራንዛክሽናቸው እንዳይገደብ የተመቻቸ ቢሆንም፣ ወደ ሀገር ቤት በሚመጡበት ጊዜ ግን ምዝገባውን እንዲያከናውኑ መክረዋል።
አቶ ሄኖክ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አገልግሎቱን በውጭ ሀገራት ለማስፋፋት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ25 በላይ በሚሆኑ ዋና ዋና ከተሞች የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ጋር የማስተሳሰር የጊዜ ገደብ እስከ ግንቦት 6 ቀን መሆኑን ያስታወቁት ኦፕሬሽን መሪው፣ ተገልጋዮች የመጨረሻውን ቀን ጠብቀው ከሚፈጠር መጨናነቅ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
” ጊዜው ሊያልቅ አንድ ቀን ሲቀረው የሚታየው ሩጫ አላስፈላጊ መጨናነቅንና በሲስተም ላይ ጫናን ያመጣል ዛሬ ይህንን መረጃ የሚሰሙ ሰዎች ጊዜ ሳይወስዱ አሁኑኑ የማስተሳሰር ስራቸውን እንዲያከናውኑ እንጠይቃለን ፣ ሂደቱ አምስት ደቂቃ እንኳን የማይወስድና በጣም ምቹ ነው ” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በመረጃዎች መካከል ልዩነት (ለምሳሌ በስም አጻጻፍ ወይም በልደት ቀን) ካለ፣ ተገልጋዮች በፋይዳ የመረጃ ማሻሻያ (Update) ስርአት በመጠቀም በፍጥነት ማስተካከል እንደሚችሉና የማስተሳሰር ሂደቱም በመላ ሀገሪቱ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መጠናቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
#Tikvah
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.