ክቡር ቴዎድሮስ ጌታቸው በኮሜሳ ፍርድ ቤት በዳኝነት ተሾሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኬንያ ናይሮቢ ስቴት ሃውስ በተከናወነ ደማቅ ስነ ስርአት ክቡር ቴዎድሮስ ጌታቸው በኮሜሳ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አማካኝነት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

ላለፉት ሁለት አመታት በአለም አቀፍ የህግ መድረኮች የህግ የበላይነትን ለማስከበርና አድሎአዊ አሰራሮችን ለመቃወም ሲደረግ የነበረው ከፍተኛ ጥረት በዚህ ሹመት በድል ተጠናቋል።

ይህ ሂደት በውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙሀንና ተቋማት ዘንድ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት የቆየ ቢሆንም በሀገር ውስጥ ግን በስፋት ሳይነገር ቆይቷል። በታህሳስ ወር በተካሄደው የኮሜሳ ሀገራት ምርጫ ኢትዮጵያዊው ባለሙያ ጥብቅ መስፈርቶችን አልፈው በከፍተኛ ድምጽ መመረጣቸው ይታወሳል።

በዚሁ የሹመት መርሃ ግብር ላይ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የዛምቢያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ብሩንዲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሲሼልስ፣ ኡጋንዳ፣ ዚምቧብዌ እና ግብፅ ተወካዮች የዳኝነት ስልጣን ተረክበዋል።

ከዚህም ባለፈ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ የቀድሞ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ውብሸት ሽፈራው የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በመሆን መሾማቸው ለሀገራችን ድርብ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።

#COMESA #Justice #EthiopianExcellence #Law #Africa #Nairobi #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: