#Ethiopia | በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስም ያላቸው የኦቦ ሌንጮ ለታ የሕይወት ታሪክን የሚተርክ መጽሐፍ ታትሞ ሊመረቅ መሆኑ ታወቀ።
በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ 501 ገጾች ያሉት ሲሆን ደራሲውና አሳታሚው ዙፋን ኡርጋ ለዝግጅቱ ሦስት ዓመታት እንደፈጀባት ገልጻለች።
እንደ መርሃ ግብሩ ከሆነ መጽሐፉ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሚመረቅበት ወቅት የባለታሪኩ ወዳጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ እንግዶች ይታደማሉ።
መጽሐፉ ኦቦ ሌንጮ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ያሳለፉትን ዘመን እንዲሁም በሀገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበራቸውን ሚና በዝርዝር የሚተርክ ነው።
በትውልዳቸው የወለጋ ደምቢዶሎ ልጅ የሆኑት ኦቦ ሌንጮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዳማ ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ አቅንተው በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መስራች ከሆኑት ቀዳሚ ግለሰቦች አንዱ የሆኑት እኚሁ አንጋፋ ፖለቲከኛ አብዛኛው የዕድሜ ዘመናቸው በትግል እና በስደት ያለፈ ነው።
በተለይም ደግሞ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር በነበረው የሽግግር መንግሥት ምስረታ ሂደት ላይ ቁልፍ ተሳታፊ እንደነበሩ ይታወሳል።
የቅርብ ወዳጆቻቸውም ባለታሪኩን ከፍተኛ የማንበብ ፍላጎት ያላቸውና ረቂቅ አእምሮ ባለቤት እንደሆኑ ይመሰክራሉ።
ይህ መጽሐፍ የቀድሞውን የትጥቅ ትግል እና የቆዩ የፖለቲካ ሂደቶችን ለመረዳት ለሚፈልጉ አንባቢዎች ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
#LenchoLeta #Biography #EthiopianPolitics #NewBook #Oromia #History #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.