ድምፃዊት ማዲቱ ወዳይ በደረሰባት የመኪና አደጋ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ተዛወረች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በተለየ የድምፅ ቀለምና በባህላዊ የሙዚቃ ስራዎቿ የምትታወቀው ድምፃዊት ማዲቱ ወዳይ ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሟታል።

አደጋው የተከሰተው ድምፃዊቷ ከኮምቦልቻ ወደ ወልድያ በመጓዝ ላይ ሳለች ስሪንቃ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ ነው።

በወቅቱ በነበረው አደጋ ከድምፃዊቷ በተጨማሪ አሽከርካሪውና ሌላ አንድ ግለሰብ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

ተጎጂዎቹ በአቅራቢያው በሚገኝ የህክምና ተቋም የመጀመሪያ እርዳታ ቢደረገላቸውም የድምፃዊት ማዲቱ ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ለበለጠ ክትትልና ህክምና በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ተደርጓል።

የጥበብ አፍቃሪዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለድምፃዊቷና አብረዋት ለነበሩት ሰዎች ፈጣን ማገገምን እንዲመኙና በየእምነታቸው ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሙያ አጋሮቿና ወዳጆቿም የህክምና ሂደቱን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።

#ማዲቱወዳይ #የጥበብሰው #የመኪናአደጋ #ጸሎት #ጤና
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: