ፍርድ ቤቶች የምክር ቤቱን ውሳኔዎችን እንደ አንድ የሕገ መንግሥት ድንጋጌ እኩል ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው ተግተው ሊሰሩ ይገባል፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ፍርድ ቤቶች የምክር ቤቱን ውሳኔዎችን እንደ አንድ የሕገ መንግሥት ድንጋጌ እኩል ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው ተግተው ሊሰሩ ይገባል፡- አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያሳልፋቸው የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔዎች፣ እንደማንኛውም የሕገ መንግሥት ድንጋጌ እኩል ተፈጻሚነትና አስገዳጅነት እንዳላቸው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር “በሕገ መንግሥት ትርጉም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣን፣ የፍርድ ቤቶች ሚና፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው” በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት አፈ ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የትርጉም ውሳኔዎች ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ በሚከሰቱ ተመሳሳይ ጉዳዮች ሁሉ ላይ ተፈጻሚ የመሆን አስገዳጅነት አላቸው ብለዋል። በመሆኑም ከምክር ቤቱ የትርጉም ውሳኔ ውጭ ውሳኔ ማሳለፍ ሕገ መንግሥቱን እንደ መጣስ እንደሚቆጠር አሳስበዋል።

አንዳንድ ፍርድ ቤቶች የምክር ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔዎች በድጋሚ የመመልከት ዝንባሌ እንደሚያሳዩ የጠቀሱት አቶ አገኘሁ፤ ይህ ድርጊት በሕግ ሥርዓቱ ላይ “እንቆቅልሽ” ከመፍጠሩም ባለፈ የሕግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው ብለዋል።

ማንኛውም ከምክር ቤቱ ውሳኔ ጋር የሚቃረን እርምጃ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9(1) መሠረት ተቀባይነት እንደማይኖረው አስታውቀዋል አፈ ጉባኤው።

የዳኝነትና የፍትሕ ተቋማት የሕገ መንግሥቱን የበላይነት የማረጋገጥ፣ የማክበርና የማስከበር ሕገ መንግሥታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

EBC






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1