#FastMereja I በሐረር ከተማ የሚገኘው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ አንዲት እናት አምስት ሕፃናትን በሰላም መገላገላቸውን አስታወቀ። ትናንት ምሽት 3፡30 ላይ በሰላም የተገላገሉት የ35 ዓመቷ ወይዘሮ በድሪያ አደም፣ አራት ወንድ እና አንድ ሴት ልጆችን ተቀብለዋል።
አምስቱም ሕፃናትና እናታቸው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የሕክምና ቡድኑ አረጋግጧል። ወይዘሮ በድሪያ የእርግዝና ጊዜያቸውን በዚሁ ሆስፒታል በቅርብ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸው ለስኬታማው የወሊድ ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል።
የሶፊ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ በድሪያ፣ ከአሁኑ የወሊድ ሂደት በፊት የሌሎች ሦስት ልጆች እናት እንደነበሩ ኢዜአ ዘግቧል።
Source: FastMereja









No comments yet.