#Ethiopia | የዓለማችንን የዜና አቀራረብ እና የሚዲያ አጠቃቀም የቀየሩት ዝነኛው ባለሀብት ቴድ ተርነር በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተቋማቸው ሲኤንኤን (CNN) አረጋግጧል።
በፈረንጆቹ 1980 የመጀመሪያውን የ24 ሰዓት የዜና ጣቢያ በመመስረት የሚታወቁት ተርነር፣ በወቅቱ የማይታሰብ የነበረውን የ”ቀጥታ ስርጭት” የዜና ጥበብ ለዓለም በማስተዋወቅ የሚዲያ ታሪክን የለወጡ ታላቅ ሰው ነበሩ።
ዜና በየሰዓቱ እና በየደቂቃው ለዓለም መድረስ እንዳለበት በማመን የመጀመሪያውን የ24 ሰዓት የዜና ኔትወርክ መስርተዋል።
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) 1 ቢሊዮን ዶላር በመለገስ በሰብአዊ መብት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ከፍተኛ አሻራ አሳርፈዋል።
ከተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በተጨማሪ በስፖርቱ ዓለምም እንደ አትላንታ ብሬቭስ ያሉ ተቋማት ባለቤት በመሆን ስማቸው ገዝፎ የሚነሳ ሰው ነበሩ።
ቴድ ተርነር በቢዝነስና በሚዲያ ዓለም ካሳዩት ብቃት ባሻገር፣ በግልጽ የመናገር ስልታቸውና በፈጠራ የታጀበ አመራራቸው በብዙዎች ዘንድ ዘላቂ ክብርን አትርፎላቸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#TedTurner #CNN #MediaIcon #Legacy #BreakingNews #RestInPeace #Ethiopia #የሚዲያ_ታሪክ
Source: GetuTemesgen







No comments yet.