በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተማሪዎች የምግብ አገልግሎትን የሚቆጣጠር ብሔራዊ ተቋም ሊመሰረት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ውሳኔው ዩ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተማሪዎች የምግብ አገልግሎትን የሚቆጣጠር ብሔራዊ ተቋም ሊመሰረት መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ውሳኔው ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ከመመገብ መደበኛ ሥራ በመውጣት በአካዳሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
በዚህም ለዩኒቨርሲቲዎቹ የምግብ አገልግሎትን ለማቅረብ የአንድ ማዕከል የግዢ፣ የዝግጅት እና የስርጭት አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል ማዕቀፍ በትምህርት ሚኒስቴር እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ዕቅድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፈው ወር መቅረቡ ታውቋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ከተሻሻለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ ከታህሳስ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ ሚኒስቴሩ የዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎትን የሚቆጣጠር ብሔራዊ የምግብ ተቋም ለማቋቋም እየተሠራ እንደሆነ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሽኔ ገልፀዋል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: