ብልፅግና ከኔ ወሰደ እንጂ እኔ ከብልፅግና ሆነ ከመንግስት ምንም ወስጄም ተጠቅሜም አላውቅም።

- Advertisement -
Sidebar AD

በረከት ገበሬዋ

ተበዳይ ዝም ካለ ተከሳሽ ይሆናል!!!!ሀይ ሀገሬ እኔ ላቤን አልነበረም የሰጠሁሽ ደሜን ነው!! እኔን አስረውኝ በስሜ ለሸጡት ነዳጅ እኔን ተጠያቂ ማድረግ ከግፍም ግፍ ነው።

ሀገሬ ግን እውነት በጣም አዘንኩብሽ ተቀየምኩሽ አፈርኩብሽ!! ከሰለጠነ ከሀብተም ሀገር መጥቼ ድቅድቅ ያለ ጫካ ገባሁ ዝቅብዬ ሰራሁ ለሴቶች እህቶቼ ኩራት ሆንኩ።

3 ትምርት ቤት ገንብቼ አቅመ ደካማ ህፃናትን አስተማርኩ ምገባ ማእከል 55 ሚሊዮን ብር ገንብቼ አረጋዊያንን ጦርኩ።የፌደራል ፖሊስ በስራ ላይ እያሉ የተጎዱ አባሎቻቸውን በአቅሜ ደገፍኩ ሐገሬ ስትፈልገኝ አጠገቧ ቆምኩ ። የቦረና ድርቅ ላይ ነበርኩ የጎፉ መሬት መንሸራተት ተሳትፌአለው ።

እናቶች እና ህፃናት በነፃ የሚታከሙበት ክሊኒክም ገንብቼ ለምስኪን ወገኖቼ አበርክቻለው። ምስኪኑ ማህበረሰብ በኑሮ ውድነት እንዳይንገለታ የምችለውን አደረኩ ይሄ ውሸት ነው ሀገሬ እስቲ ልጠይቅሽ???? ለምን በውሸት ከሰስሺኝ ????ከመንግስት ጎን የቆምኩት እኮ የተሻለች ኢትዮዸያን አያለው በሚል ተስፉ እንጂ ስላገኘው ስለተጠቀምኩ አይደለም ።

አንድ ስንዝር የከተማ መሬት እንኳን ጠይቄ ወስጄ አላውቅም ሀገሬ እውነት በጣም ተቀየምኩሽ!! ከጉድለቴ ሰጠሁሽ እንጂ 1 ብር አልነጠኩሽም በነብሴ ምላለው እግዚያብሄር ይመስክርብኝ እንዳልሰራ ከፈለግሽ ካልፈለግሺኝ ምናለበት ከነ ሙሉ ክብሬ ወደ መጣሁበት ብትሸኚን ያለ ስሜ ስም ሰጠሺኝ እኔ አረግምሺም ከዚ በፊት በዙ ጀግኖች ብዙ የደከሙልሽ ውለታቸውን ስለበላሽ ረግመውሻል ያ በቂ ነው !! የልጆች እናት እንደሆንኩ እያወቁ ህግ እንዲያስከብሩ ህዝብ እና መንግስት አምኖ ያስቀመጣቸው ግለሰቦች በሴትነት ክብሬ መጡብኝ ሰው ሀገር ለፍቼ ያመጣሁትን ገንዘቤን ያለ አግባብ ቀሙኝ እና ሀገሬ ለኔ ይሄ ይገባኛል እንዴ ??? የራሳቸውን የሚዲያ ሰራዊት አዘነቡብኝ ፍርድ ቤት 14 ግዜ ቀርቤአለው 7 ግዜ ዳኞች እንድፈታ አዘዋል። እኔ እዚ ሀገር የመጣሁት ህግ እና መንግስት አለ ብዬ ነው።

ማክበር የሴቶችን ቀን ሳይሆን እራሳቸው ሴቶችን ነው!!!!!!




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: