#FastMereja I ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ ዮሰን ጌታሁን፣ በአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ስራ ላይ ያለውን የሃሳብ ልዩነት ገለጸ።
ድምጻዊው “ሀገር የሞተችበት የት ሄዶ ያለቅሳል” የሚለው የቴዲ አፍሮ ግጥም እንደማይስማማው የገለጸ ሲሆን፣ ይህን ሃሳብ በመቃወሙ ቅር የተሰኙ ወገኖች መኖራቸውን ጠቁሟል።
ቴዲ አፍሮ “ሀገር የሞተችበት…” ሲል እኔ ደግሞ “ሀገሬ አልሞተችም፣ አለች” ብዬ አምናለሁ፤ ኪነ-ጥበብ ለቴዲ እንደፈቀደችለት ሁሉ ለእኔም ሃሳቤን የመግለጽ መብት ትሰጠኛለች ብሏል።
የግል ጥላቻ የለም፡ ከቴዲ አፍሮ ጋር ምንም ዓይነት የግል ቅሬታ እንደሌለውና እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አድናቂውና ወዳጁ መሆኑን ተናግሯል።
ቅሬታው በአርቲስቱ ማንነት ላይ ሳይሆን በአልበሙ ውስጥ በተገለጸው “ሀገር ሞታለች” በሚለው የሃሳብ ፍሰት ላይ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።
Source: FastMereja









No comments yet.