የአንድ ወጣት መታሰቢያ ለብዙዎች ተስፋ ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD

📌የኢዮብ ተስፋ ድርጅት የ27 ሚሊዮን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

​#Ethiopia | በድንገተኛ የልብ ሕመም ሕይወቱ ያለፈውን ወጣት ኢዮብ አበባውን ለመዘከር የተቋቋመው “ኢዮብ ተስፋ ለሕጻናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት”፣ በኢትዮጵያ የልብ ሕመም ላለባቸው ሕፃናትና ወጣቶች የሚውሉ የ180 ሺህ ዶላር (ከ27.5 ሚሊዮን ብር በላይ) ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁሶችን ለሦስት የጤና ተቋማት አስረከበ።

​ድርጅቱ ያሰባሰባቸውን ነፍስ አድን ቁሳቁሶች ለሚከተሉት ተቋማት በስጦታ አበርክቷል፦

-​ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

-​ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ

-​ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል

​የድርጅቱ መሥራችና የኢዮብ አባት የሆኑት አቶ አበባው አንበሳው እንደገለጹት፣ ቁሳቁሶቹ የተገኙት ከድርጅቱ ደጋፊዎችና ከታዋቂው የሜድትሮኒክ (Medtronic) ኩባንያ ጋር በተደረገ ትብብር ነው። ድርጅቱ ከተመሠረተባቸው አራት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ዘርፍ ላይ በርትቶ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን በልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ብቻ የ100 ሕፃናትን ሕክምና በቀጥታ መደገፍ ችሏል።

አቶ አንበሳው ​”የልጃችንን ሕይወት በድንገት ብናጣም፣ የእሱን ስም ይዘን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን ልብ ለመጠገንና ተስፋ ለመስጠት እየሠራን እንገኛለን”ብለዋል።

​የሆስፒታሎቹ ኃላፊዎች ድጋፉ ለታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት በእጅጉ እንደሚያሳልጥ ገልጸው፣ ለድርጅቱ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ድርጅቱ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ግለሰቦችና ተቋማት ለዚህ በጎ ተግባር እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#ኢዮብተስፋ #የልብሕክምና #በጎአድራጎት #ኢትዮጵያ #EyobTesfa #HeartHealthEthiopia #Charity






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: