#Ethiopia | በአዲስ አበባ እና በቡርሳ ከተሞች መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የቢዝነስ ለቢዝነስ (B2B) የውይይት መድረክ በስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል፡፡
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ 160 የሚሆኑ የቱርክ ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አባል የሆኑ በርካታ ድርጅቶችም ተገኝተው የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል፡፡
ይህ የሻጭና ገዥዎችን ትሥሥር የሚያጠናክረው መድረክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በቱርክ መንግሥት፣ በአዲስ ቻምበር እና በቡርሳ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ተብሏል፡፡
በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር መለስ ዓለም፣ አዲስ ቻምበር የሁለትዮሽ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲያድግ የሚያደርገው ጥረት በመንግሥት ዘንድ ትልቅ እውቅና እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡
የቡርሳ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ቡርካይ በበኩላቸው፣ ከተማቸው ቡርሳ በቱርክ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የንግድ ማዕከላት አንዷ መሆኗን ጠቅሰው፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በሕንፃ ግንባታ፣ በቤት ቁሳቁስና በኬሚካል ኢንዱስትሪ የተሰማሩ የቡርሳ ነጋዴዎች ከኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡
#ንግድ #ኢንቨስትመንት #ኢትዮጵያ #ቱርክ #አዲስቻምበር #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.