የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር የተመሰረተበትን 60ኛ አመት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበረ!!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሚያዝያ 27 ቀን 2018ዓ.ም አዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የማህበሩ አባት ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ተከብሯል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትና ማህበሩ ከምስረታው ጀምሮ ያሳለፋቸውን ደማቅ አሻራ ለሀገሪቱ የፍትህ መጎልበት ከህግ ማርቀቅ ጀምሮ በኢትዮጵያ ትልቅ አበርክቶ እንደነበርና የማህበሩ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ወንድማገኝ ገ/ስላሴ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ዶ/ር ፍቅር ሙሉጌታ የመክፈቻ ንግግር አድርዋል።

በመቀጠልም የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክቡር ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረትና የኢፌዴሪ FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
ክብርት ወ/ሮ ሀና አርዓያስላሴ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ማህበሩ ባለፉት 60 አመታት በትውልድ ቅብብሎሽ በርካታ ስራዎችን መስራቱን በመግለፅ ለወደፊቱም በተጠናከረ መልኩ ለህግ የበላይነት መረጋገጥና መስፈን በጋራ እንሰራዋለን በማለት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ንግግር አድርገዋል።

በዝግጅቱ ላይ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ደረሰና ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ Meseret Ayalew እንዲሁም የአፍሪካ ጠበቆች ህብረት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ Tewodros Getachew TP ተገኝተዋል።

በመቀጠልም በእውቅናና ሽልማት ኮሚቴ የተዘጋጀውን ልዩ ልዩ ሽልማት ለማህበሩ ቀጣይነት መረጋገጥ በርካታ ተግዳሮቶችን በማለፍ አበርክቶ ላደረጉ በህይወት የሌሉም እና አሁንም እያገለገሉ ላሉ የምስጋናና ዕውቅና ሽልማት ፕሮግራም ተከናውኗል።

በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ ከጠበቆች ማህበር ባለፈ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት አንጋፋ የህግ ምሁራን ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ ፕሮፌሰር ሙራዶ አብዶ እና ዶ/ር ዘካሪያ ቀንዓ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወጣት የህግ ባለሙያዎች ልዩ አበርክቶ የነበራቸው ጠበቃ የህግ አማካሪ ክብርት ወ/ሮ Liya Terefe Melkamu Ogo Metassebia Hailu እንዲሁም ከ5 በላይ የህግ መፃፎችን ለህግ ባለሙያና ለፍትህ ስርዓቱ መሻሻልና እድገት በማሳተም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የነበራቸው Federal First Instance Court Of Ethiopia ዳኛ የሆኑት አቶ ካሴ መልካም የልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

በስተመጨረሻም ማህበሩን ለማጠናከር ሁሉም የህግ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር – Ethiopian Federal Bar Association አባላት የበኩላቸውን በገንዘብና በእውቀት እንዲያግዙ ስምምነት ላይ በመድረስ የተጠናቀቀ ሲሆን
የእራትና የምሳ ፕሮግራም ተከናውኖ የእለቱ ፕሮግራም ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል።
🙏👏






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1