የኤሌክትሪክ ወርሃዊ ክፍያ ላይ የተደረገ የታሪፍ ጭማሪ አለመኖሩ ተነገረ
ካለፉት 3 ወራት ወዲህ በኤሌክትሪክ ወርሃዊ ክፍያ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መደረጉን ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለጣቢያችን ብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በጉዳዩ ዙሪያ ብስራት ሬዲዮ ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማርኬቲንግ ፣ሽያጭ እና የደንበኞች አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ደንድር ወርሃዊ ክፍያ አጠቃቀምን መሠረት አድርጎ በተቀመጠዉ መደብ ዉስጥ ያለዉ ታሪፍ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል ።
ባለፈዉ ወር 100 ኪሎ ዋት የተጠቀመ ደንበኛ በዚህም ወር 100 ኪሎ ዋት ቢጠቀም በየሩቭ ዓመቱ ከሚጨምረዉ ታሪፍ ዉጪ ሌላ ተጨማሪ ጭማሪ እንደማይኖር አቶ ኢሳያስ ጨምረዉ ገልፀዋል ።
ከንባብ ጋር በተያያዘ ብዙ ስራ እየተከናወነ ቢሆንም የተወሰኑ ክፍተቶች መኖራቸዉን የገለፀዉ አገልግሎቱ እነዚህን ክፍተቶች ለማስተካከል ደንበኞች ቤታቸዉ ሆነዉ ንባብ መላክ የሚችሉበትን የቴሌግራም ቦት ስርዓት በሁሉም ሪጅንኞች ተግባራዊ መደረጉን አስታውቋል ።
በ5 ዓመት ጊዜ ዉስጥ 4.65 ሚሊዮን ቆጣሪዎችን ወደ ስማርት ለመቀየር መታቀዱን የገለፁት አቶ ኢሳያስ እስከ እዛ ባለዉ ጊዜ ዉስጥ የድህረ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች እንዲከፍሉ የሚጠበቀዉ አጠቃቀማቸዉን መሠረት ያደረገ ክፍያ ብቻ ነዉ ብለዋል ።
ጭማሪ ተደርጎብናል የሚሉ ደንበኞች ካሉ በንባብ ስህተትም ይሁን ሳይከፈል የተጠራቀመ ኖሮ ከሆነ ማየት እንደሚቻል ተገልጿል ።
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.