እየተዝናኑ ለወገን ደራሽ ይሁኑ

- Advertisement -
Sidebar AD

ለኪነ ጥበብ ባለሙያው ሞቱማ ተርፋሳ የተዘጋጀ የረድኤት የቴአትር ምሽት

#Ethiopia | በከባድ የልብ ህመም ምክንያት የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልገው ለወጣቱ የጥበብ ሰው ሞቱማ ተርፋሳ የሙያ ባልደረባዎቹ አጋርነታቸውን ለመግለጽ ልዩ የቴአትር መርሃ ግብር አዘጋጅተዋል።

አንጋፋው መራሄ ተውኔት ማንያዘዋል እንደሻው ያዘጋጀው የመስቀል ወፍ የተሰኘው ተወዳጅ መድረክ ተውኔት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአዳማ ሲኒማ እሊያድ ለታዳሚ ይቀርባል።

ይህ ተውኔት በበርናርድ ስሌድ ተጽፎ በአንዱዓለም ውብሸት (አቡቲ) ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲሆን፣

መስከረም አበራ፣
አልዓዛር ሳሙኤል፣
ህሊና ሲሳይ እና
አለምሰገድ አሰፋ ያሉ ታዋቂ ተዋንያን በመድረክ ላይ ብቃታቸውን ያሳዩበታል።

የዝግጅቱ ረዳት አዘጋጅ ራሱ ህመሙን እየተጋፈጠ ያለው ሞቱማ ተርፋሳ በመሆኑ፣ የእርስዎ መገኘት ለኪነ ጥበብ ባለሙያው ህይወት መትረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ሁላችንም
ቅዳሜ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሲኒማ እሊያድ በመገኘት ጥበባዊ እርካታን እያገኙ ወገናዊ አጋርነትዎን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።

#ArtForACause #HelpMotuma #EthiopianTheatre #Adama #SupportArtists #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: