የታሪፍ ማሻሻያ አልተደረገም፤ በዘፈቀደ ዋጋ የሚጨምሩ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተገን በማድረግ፣ በራስ ፍላጎት የታሪፍ ጭማሪ የሚያደርጉ አሽከርካሪዎችና የትራንስፖርት ማኅበራት ድርጊት “ሕገ-ወጥ” መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
​ቢሮው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን ተከትሎ የጥናት ሥራ እያከናወነ ቢሆንም፣ እስካሁን ግን ምንም ዓይነት ይፋዊ የታሪፍ ማሻሻያ አለመደረጉን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ገልጸዋል።

እንደ ባለሥልጣኑ ገለጻ፣ ከወር በፊት የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አስቀድሞ ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ፣ አሁን ላይ ተለዋጭ ዋጋ መጨመር ተገቢ አይደለም።

​ቢሮው በጉዳዩ ላይ ያስተላለፋቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

-በዘፈቀደ ዋጋ በሚጨምሩ አሽከርካሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በባለንብረቶችም ላይ ጠንካራና አስተማሪ እርምጃ ይወሰዳል።

​-ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የሚደረገው የመስክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

– የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍና ፍላጎትን ለማመጣጠን ተጨማሪ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና የኤሌክትሪክ ባሶች በስፋት እንዲሰማሩ እየተደረገ ይገኛል።

-ተጠቃሚዎች ከተቀመጠው ታሪፍ በላይ የሚጠይቁ አሽከርካሪዎችን ሲያጋጥሟቸው በነፃ የጥሪ መስመር 9417 ላይ ደውለው ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

​የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ የነዳጅ ዋጋ መናር በኅብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥናት እያደረገ ቢሆንም፣ የጥናቱ ውጤት ታውቆ ይፋዊ መመሪያ እስካልወጣ ድረስ ነባሩ ታሪፍ ተፈጻሚነቱ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#Ethiopia #AddisAbaba #TransportTariff #FuelPrice #PublicTransport #ElectricBuses #TrafficRegulation


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1