#Ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል አዘጋጅነት በየሳምንቱ ረቡዕ የሚካሄደው የአንድ ግጥም አንድ ወግ መርሃ ግብር በ54ኛው ሳምንት ዝግጅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን በክብር እንግድነት ጋብዞ አቆይቷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት አቶ መስፍን ከተማሪነት ጊዜያቸው አንስቶ የአየር መንገዱ ከፍተኛ መሪ እስከሆኑበት ጊዜ ድረስ ያለውን አነቃቂ የሕይወት ጉዞና የሥራ ልምድ ለተማሪዎችና ለታዳሚው አጋርተዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 75 ዓመታት ለሀገሪቱ ተቋማት ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
አያይዘውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በምርምርና በተለያዩ የልማት ዘርፎች በጋራ ለመሥራት እንዲሁም ተቋሙን በልዩ ልዩ መስኮች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የአቶ መስፍን ጣሰው በዝግጅቱ ላይ መገኘት ለተማሪዎች ትልቅ የሞራል መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸው በአየር መንገዱና በዩኒቨርሲቲው መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው አረጋግጠዋል።
#አዲስአበባዩኒቨርሲቲ #የኢትዮጵያአየርመንገድ #አቶመስፍንጣሰው #የአንድግጥምአንድወግ #ኪነጥበብ #ትምህርት #መሪነት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.