የደረጃ እድገት ተፈቀደየአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የማስተማር ስነ-ዘዴ ስልጠና ላልጨረሱ መምህራን የደረጃ እድገት እንዲሰጥ ፈቀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የደረጃ እድገት ተፈቀደ‼️
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የማስተማር ስነ-ዘዴ ስልጠና ላልጨረሱ መምህራን የደረጃ እድገት እንዲሰጥ ፈቀደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ የማስተማር ሙያ ስልጠና (PGDT) ባለመውሰዳቸው ወይም ባለማጠናቀቃቸው ምክንያት የደረጃ እድገታቸው ተቋርጦ ለቆዩ መምህራን፣ ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የደረጃ እድገት እንዲሰጥ መወሰኑን አስታወቀ።
ቢሮው ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው፤ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ መምህራን በሙያ ስልጠና መታገዝ ቢኖርባቸውም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ስልጠናውን ሳይወስዱ በመቆየታቸው የደረጃ እድገታቸው ተቋርጦ መቆየቱን ገልጿል።
ቢሮው የትምህርት ሴክተሩ ለየትምህርት ደረጃው የተዘጋጀውን ፕሮፋይል እና ብቃት የሚያሟሉ መምህራንን በማፍራት ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት የተለያዩ ስልጠና መርሃ-ግብሮችን በመቅረጽ እየተገበረ መሆኑ ገልጿል።
ከነዚህም መካከል በቅድመ ሥራ እና በሥራ ላይ የሚሰጥ የማስተማር ስነ-ዘዴ ስልጠና (PGDT) ሲሆን የስልጠናውን አሰጣጥ ከመምህራን ደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ጠቅሷል።
በእዚህም ምክንያት ያልሰለጠኑ መምህራን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄድ እንዲሁም ስልጠናው ከተጀመረበት ጊዜ በኋላ የደረጃ እድገት ጊዜያቸው እና ስልጠናው የሚፈጀው ጊዜ አለመጣጣም መፍጠሩን በደብዳቤው ተገልጿል።
በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት የደረጃ እድገት ተጠቃሚ የሚሆኑት መምህራን በአራት ዋና ዋና ዘርፎች ተከፍለዋል ፡-
1. በዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ እያሉ የማስተማር ስነ-ዘዴ (PGDT) ስልጠና ያልጀመሩ ወይም ያላጠናቀቁ መምህራን።
2. በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማሩ ነገር ግን በዲፕሎማ የሙያ ማረጋገጫ ያላቸው መምህራን።
3. በማንኛውም የትምህርት አይነት ተመርቀው በስራና ተግባር ትምህርት ላይ የተሰማሩና በዲፕሎማ የማስተማር ሙያ የሰለጠኑ።
4. በአፕላይድ ሳይንስ ቀጥታ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው በማስተማር ሙያ ስልጠና ያልወሰዱ ሆነው በተከታታይ ዓመታት በማስተማር ሙያ ላይ የነበሩና የቀጣይ የደረጃ እድገት የሚጠባበቁ መምህራን ናቸው።
ቢሮው አክሎም፣ እነዚህ መምህራን ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ እድገት እንዲሰጣቸው ቢወሰንም፤ በቀጣይ የሚኖራቸው የደረጃ እድገት ግን የግድ የPGDT ስልጠናን ወይም ተመጣጣኝ የሙያ ስልጠናን ማጠናቀቅ ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን አሳስቧል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1