በፌደራል ፖሊስ እና በባለሀብቷ በረከት ወርቁ መካከል ያለው ውጥረት አይሏል! ባለሀብት በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ) በወንጀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በፌደራል ፖሊስ እና በባለሀብቷ በረከት ወርቁ መካከል ያለው ውጥረት አይሏል!
ባለሀብት በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ) በወንጀል መፈለጓን ተከትሎ ከባድ ውንጀላዎችን የሰነዘረችበት ምላሽ ሰጥታለች።
ባለሀብቷ ከእርሻ ስራዋ ወጥታ ወደ ወርቅ ማዕድን ዘርፍ መግባቷን እንደምትቆጭ ገልጻ፣ ስምንት ሚሊዮን ብር ሀገር አሳጣሽ መባሏን በማጣጣል “እናንተ ራሳችሁ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወስዳችሁብኛል” ስትል ስማቸውን ያልጠቀሰቻቸውን አካላት ወንጅላለች።
በተጨማሪም የተፈቀደላትን ነዳጅ እንዳልወሰደችና ሌሎች አካላት ሸጠው እንደበሉት በመጥቀስ፣ ድርጊቱ እሷን ከመንገድ ለማስወገድ የተጠነሰሰ ሴራ እንደሆነ ገልጻለች።
ባለሀብቷ አብሮት ስሙ የተጠቀሰው አቡሽ አየለ 28 የሚደርሱ የወርቅ ማውጫዎች ያሉትና ለብሔራዊ ባንክ በኩንታል ወርቅ የሚያስገባ መሆኑን በመጥቀስ፣ በወርቅና ነዳጅ ዘርፍ ያሉ ጥቂት ቡድኖች ሌሎች ተወዳዳሪዎች እንዲወገዱ እያደረጉ ነው ስትል ተናግራለች።
“መጨረሻውን አብረን እናያለን” በሚል መልእክት ምላሽዋን የደመደመችው በረከት ወርቁ፣ ከዚህ ድርጊት ጀርባ ያሉ ግለሰቦች እጃቸውን እንዲሰበስቡ አሳስባለች።
በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በፖሊስ የክትትል ሂደት እና በባለሀብቷ የመከላከል ምላሽ መካከል ሆኖ ከፍተኛ ህዝባዊ ትኩረትን ስቧል።#ጉርሻ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2