ሰበር ዜና
በቴህራን ሰማይ ላይ ፍንዳታዎች ተሰሙ፤ የኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓት ጥቃት እየመከተ መሆኑ ተገለጸ
በኢራን መዲና ቴህራን እና በምዕራባዊ የከተማዋ ክፍሎች በርካታ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ሥርዓት ወደ ሥራ መግባቱን የኢራን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ የኢራን መከላከያ ኃይሎች “ጠላት” ሲሉ የጠሯቸውን ኢላማዎች ለመምታትና የአየር ጥቃቱን ለመመከት አጸፋዊ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። ፍንዳታዎቹ በመላው መዲናዋ የተሰሙ ሲሆን፣ የጥቃቱ ምንጭ እና የደረሰው ጉዳት እስካሁን በዝርዝር አልታወቀም።
በመላው መካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበት በዚህ ወቅት፣ በቴህራን የተሰሙት ፍንዳታዎች ቀጠናውን ይበልጥ ስጋት ላይ ጥለውታል።
@seledadotio

No comments yet.