በትግራይ 6 ሺ ድርጅቶች ተዘግተው
100 ሺ ሠራተኞች ተበትነዋል -ቢሮው
በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት ተቋቁመው ይንቀሳቀሱ የነበሩ 95 በመቶ የሚሆኑ የንግድ ድርጅቶችና ኢንዱስትሪዎች መውደማቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ይፋ አደረገ። ቢሮው እንዳስታወቀው፣ የግጭት ማቆም ስምምነቱ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ባለመሆኑ ምክንያት ከ100 ሺሕ በላይ ሠራተኞችን የቀጠሩ ከ6 ሺሕ በላይ ድርጅቶች ተዘግተው ይገኛሉ። ዘርፉ በእዳ ጫና፣ በነዳጅና ጥሬ ዕቃ እጥረት፣ እንዲሁም በመሠረተ ልማት ውድመት ሳቢያ እስካሁን ማገገም እንዳልቻለ ተገልጿል።
ምንም እንኳ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የኢንዱስትሪ ቢሮው ችግሩ እንዲፈታና የባንክ ብድሮች እንዲሰረዙ ለፌዴራል መንግሥት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ተጨባጭ መፍትሄ አለመገኘቱን ገልጸዋል። በፋይናንስና በንግድ ገደቦች ሳቢያ የክልሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ክፉኛ መጎዳቱን የጠቀሰው ቢሮው፣ ከፌዴራል ባለሥልጣናት ጋር የተደረጉ ውይይቶችም የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጡ አስታውቋል።

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.