ኢማኑኤል ማክሮን ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሊመጡ ነው
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለስራ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ መሆኑ ተዘግቧል
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኬንያ ናይሮቢ የሚካሄደውን “አፍሪካ ፎርዋርድ” ጉባኤ ካጠናቀቁ በኋላ፣ በመጪው ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለአጭር የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።
ፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት በጥንቃቄ የተመረጡ የፈረንሳይ ግዙፍ ኩባንያዎች መሪዎችን በማስከተል ሲሆን፣ ጉብኝቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው ይላል የካፒታል ዘገባ።
በፕሬዝዳንቱ የታጀበው ልዑክ እንደ ካርፉር ያሉ ታዋቂ የችርቻሮ ንግድ ተቋማትን እና ሜሪዲያም የተሰኘውን የኢንቨስትመንት ድርጅት አመራሮችን ያካተተ ሲሆን፣ በተለይም ካርፉር ከኢትዮጵያው ሚድሮክ ጋር በፈጠረው የፍራንቻይዝ ስምምነት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ማቀዱ የጉብኝቱ አንዱ ዋነኛ ትኩረት መሆኑ ተጠቁሟል።
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.