ኮሜርሻል ኖሚኒስ 60ኛ ዓመቱን በአዲስ ራዕይ አከበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል አክብሯል። ተቋሙ በበዓሉ አጋጣሚ ወደ ውጭ ሀገር የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሪል ስቴት እና የኤሌክትሪክ መኪና ግብይትን ጨምሮ በበርካታ አዳዲስ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ 60ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የዕውቅና እና የምስረታ በዓል መርሃ-ግብር ላይ እንደገለጸው፣ ተቋሙ ራሱን በአዲስ መልክ በማደራጀት ስትራቴጅያዊ ለውጦችን እያደረገ ይገኛል። እስካሁን በሀገር ውስጥ ብቻ የተገደበውን የሰው ኃይል አቅርቦት አገልግሎት ወደ ውጭ ሀገራት ለማስፋፋት የወሰነ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም በሪል ስቴት፣ በልብስ ነክ ምርቶች፣ በኬሚካሎች፣ በተቀናጀ የቆሻሻ አወጋገድ እና በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ላይ በስፋት ለመሰማራት አቅዷል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ እንደገለጹት፣ ይህ የማስፋፊያ ዕቅድ የተቋሙን ተደራሽነት ከሀገር ውስጥ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያለመ ነው። ተቋሙ በፋይናንስ ረገድም ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም 2.6 ቢሊዮን ብር የነበረው ገቢው፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 5.6 ቢሊዮን ብር ማደጉን አስታውቀዋል። አዳዲስ የስራ ዘርፎች መጀመራቸው ይህን ገቢ ይበልጥ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

በአሁኑ ወቅት ከ42 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረው ኮሜርሻል ኖሚኒስ፣ ከ50 በላይ በሚሆኑ የሙያ ዘርፎች የሰው ኃይል እያቀረበ ይገኛል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: