የዓለም ጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ
በአንድ የቱሪስት መርከብ ላይ በደረሰ የሀንታ ቫይረስ ወረርሽኝ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ተጨማሪ ተጠቂዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በባሕር ላይ በሚጓዝ የቱሪስት መርከብ ውስጥ የተከሰተው ይህ ወረርሽኝ ለሦስት ተሳፋሪዎች ሞት ምክንያት ሆኗል።
ድርጅቱ አክሎም፤ከሟቾቹ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሌሎች ሰዎች ላይም የቫይረሱ ምልክቶች ሊታዩ እንደሚችሉ ስጋቱን ገልጿል።
ይሁን እንጂ፤አስፈላጊው የጥንቃቄ እርምጃዎች በአግባቡ ከተወሰዱ የወረርሽኙን ስርጭት መገደብና በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል ድርጅቱ አስታውቋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ተሳፋሪዎችና የጉዞው አዘጋጆች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ሀንታ ቫይረስ አብዛኛውን ጊዜ ከአይጥ ዝርያዎች ወደ ሰው የሚተላለፍ ከባድ የጤና ችግር ሲሆን፣ ድርጅቱ የወረርሽኙን አድማስ ለማጥበብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል ሲል የዘገበው TRT WORLD ነው።
@seledadotio

No comments yet.