ታዋቂው የፒያኖ ተጫዋች ግርማ ይፍራሸዋ በአዲስ አበባ ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአውሮፓና በአሜሪካ ታላላቅ መድረኮች ላይ ስራዎቹን በማቅረብ አለምአቀፍ እውቅናን ያተረፈው የፒያኖ ተጫዋችና አቀናባሪ ግርማ ይፍራሸዋ በኢትዮጵያ ልዩ የሙዚቃ ድግስ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል።

ሙዚቃ ለሰብአዊነት በሚል መሪ ቃል የሚቀርበው ይህ ኮንሰርት የአዲስ አበባ ምዕራብ ሮታሪ ክለብ የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ነው።

በዝግጅቱ ላይ የምዕራባውያን ክላሲካል ሙዚቃዎች ከሀገራችን የዜማ ስልቶች ጋር ተዋህደው ለታዳሚው የሚቀርቡ ሲሆን በኪነጥበብ አማካኝነት የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳትና ለሰብአዊነት ድጋፍ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ምሽት ነው።

ይህ ልዩ ጥበባዊ ዝግጅት አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ከምሽቱ 11 ሰዓት ከ30 ጀምሮ የሚከናወን ይሆናል።

ለዝግጅቱ መግቢያ የሚሆኑ ትኬቶችን በቻፓ ድረገጽ አማካኝነት መግዛት የሚቻል ሲሆን ስለ አርቲስቱና ስለ ሮታሪ ክለብ ተጨማሪ መረጃዎችን ከተያያዙት የድረገጽ አድራሻዎች ማግኘት ይቻላል።

#ግርማይፍራሸዋ #የፒያኖሙዚቃ #ሮታሪክለብ #ሰብአዊነት #ኪነጥበብ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2