#Ethiopia | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ እንደገለጹት የሀገሪቱ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸውና ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው መስኮች መካከል አንዱ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ እንደተጠቆመው የሪፎርሙ ቀዳሚ ተግባር በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ውስጥ የነበሩ ተቋማዊ ችግሮችን በመለየት ተገቢውን መፍትሄ መስጠት ነበር፡፡
በተለይም የይዘት ጥራትን ማሻሻልና ብዝሀነትን ማረጋገጥ፣ ተቋሙን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የህትመት ውጤቶችን ተደራሽነትና ስርጭት ማሳደግ እንዲሁም ዘመናዊ አደረጃጀትና መዋቅር መፍጠር የሪፎርሙ ዋና ዋና ግቦች ነበሩ፡፡
እነዚህ በመንግስት የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት ከዘርፉ እድገት ባለፈ የሀገሪቱን የጋራ ትርክት በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተመላክቷል፡፡
#የኢትዮጵያፕሬስድርጅት #ሚዲያ #ህትመት #ሪፎርም #የሚዲያእመርታ #መረጃ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.