በስዊድን የሚኖሩ ትግራዋይ ዲያስፖራዎች በሳውዲ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በሳውዲ ዓረቢያ በሞት ፍርድ ጥላ ስር የሚገኙ በርካታ ትግራዋይ ተወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ህይወት እንዲተርፍ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በስዊድን ስቶክሆልም ተካሄደ።

​በስዊድን የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሳውዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት፣ በሞት ፍርድ ለሚጠባበቁ ወገኖቻቸው ምሕረት እንዲደረግላቸውና “የሞት ፍርድ” ቅጣት እንዲቆም ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሰልፈኞቹ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የንጹሃንን ህይወት ለመታደግ ጣልቃ እንዲገባም ጠይቀዋል።

​በሳውዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን፣ እስካሁን የሦስት ሰዎች የሞት ቅጣት መፈጸሙን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መዘገባቸው ይታወሳል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: