#Ethiopia | ቤዝ ሪል እስቴት በዘርፉ አዲስ አሠራርን በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል።
ተቋሙ ህልምዎን በወራት በሚል መሪ ቃል ግንባታቸውን በራሱ ሙሉ የፋይናንስ ወጪ ሲያከናውናቸው የቆዩትን መኖሪያ ቤቶች በ16 ወራት አጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለባለቤቶቹ ቁልፍ አስረክቧል።
ይህንን ፕሮጀክት ልዩ የሚያደርገው ቤቶቹ ሙሉ ለሙሉ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ በመሆናቸው ገዢዎች ምንም ዓይነት ተጨማሪ ወጪ ወይም እንግልት ሳይገጥማቸው ወዲያውኑ ወደ መኖሪያቸው መግባት መቻላቸው ነው።
ቤቶቹ በዘመናዊነታቸው፣ በጥራታቸውና ለሚኖሩባቸው ሰዎች ምቹ ሆነው መገንባታቸው ተገልጿል።
ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአለም ባንክ አካባቢ በተከናወነው የምረቃና የርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የቤት ገዢዎች፣ የኩባንያው አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በወቅቱም ፕሮጀክቱ ለከተማዋ የመኖሪያ ቤት ልማት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ተወድሷል።
የኩባንያው መስራችና ባለቤት አቶ ኡስማን ኑርሁሴን በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ ውጤት የኩባንያውን ጠንካራ የፋይናንስ አቅም የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ደንበኞች ስለ ዋጋ ንረት ሳይሰጉና ሳይጨነቁ ቤታቸውን በወቅቱ እንዲረከቡ አስችሏል ብለዋል።
ሪል እስቴቱ በዚህ ዙር በአለም ባንክ አካባቢ የገነባቸውን 32 ቤቶች ያስረከበ ሲሆን፣ ወደፊትም የተሻሉ ፕሮጀክቶችን በማቅረብ የደንበኞችን እምነት ለማስጠበቅ እንደሚሠራ አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ የመኪና ማቆሚያ፣ አረንጓዴ ስፍራ፣ የ24 ሰዓት የደህንነት ጥበቃና ሌሎች ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው።
#realestate #housing #ethiopianews #development #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.