የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሀገራዊ ለውጡ አማካኝነት አዲስ ህይወት መዝራቱ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የተከናወነው ሀገራዊ ለውጥ በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ላመጣው ምቹ ሁኔታ ምስጋና ይግባውና አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዳግም መወለዱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ እንደተገለጸው ተቋሙ ከለውጡ በፊት ደቅኖበት ከነበረው የመፍረስ አደጋ ወጥቶ አሁን ላይ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ኢዜአ ቀደም ሲል በሥራ ባህል መላላት፣ በቴክኖሎጂ ኋላ ቀርነትና በአሰራር ክፍተቶች ሳቢያ ተዳክሞ የቆየ ቢሆንም በሪፎርሙ አማካኝነት በሕግ፣ በአደረጃጀትና በዕሳቤ እንዲዘምን ተደርጓል።

በዚህም የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ ቁጥር ከ14 ወደ 38 ከፍ ማለቱና ተደራሽነቱም እስከ 700 ወረዳዎች መድረሱ ተገልጿል።

በተጨማሪም የቋንቋ ብዝሃነቱን በማሳደግ በ8 የአገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች መረጃ ማሰራጨት የጀመረ ሲሆን ከ30 በላይ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር አጋርነት ፈጥሯል።

ተቋሙ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር በቀን እስከ 250 የሚደርሱ ይዘቶችን እያመረተ ይገኛል።

በተለይም የአፍሪካን ትርክት ለመገንባት ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (POA) የተሰኘ ሚዲያ እውን በማድረግ አህጉራዊ ተጽዕኖውን እያሳደገ መሆኑ ተጠቅሷል።

በቀጣይም ኢዜአንና ፐልስ ኦፍ አፍሪካን ( POA) በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የመረጃ ምንጭ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።

#ኢዜአ #መገናኛብዙኃን #ሪፎርም #አፍሪካ #ዜና #መረጃ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2