“ሀገሬን ትቼ የትም አልሄድም” በፖሊስ የምትፈለገው በረከት ገበሬዋ ምላሽ ሰጠች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ “በከባድ ወንጀል ይፈለጋሉ” ተብለው ፎቶግራፋቸው ይፋ ከተደረገ ግለሰቦች መካከል አንዷ የሆነችው በረከት ገበሬዋ፣ የቀረበባት ክስ እንደማታውቅና አሁንም በሀገር ውስጥ እንደምትገኝ ገለጸች። በረከት ዛሬ በቲክቶክ ማህበራዊ ገጽ በነበራት የቀጥታ ስርጭት ቆይታ፣ በፖሊስ መፈለጓን የሰማችው በማህበራዊ ሚዲያ መሆኑንና እስካሁን ምንም ዓይነት መደበኛ መጥሪያ እንዳልደረሳት ተናግራለች።

​በቀጥታ ስርጭቱ ወቅት በረከት እንደገለጸችው፣ በአሁኑ ሰዓት ያለችው በመኖሪያ ቤቷ መሆኗን አከባቢውን በቀጥታ ስርጭት በቪዲዮ ጭምር አሳይታለች። “ልጆቼ እዚህ እየተማሩ ነው፤ እኔም ሀገሬን ትቼ የትም አልሄድም” ስትል የተናገረችው ግለሰቧ፣ አድራሻዋ ለሚመለከተው አካል ግልጽ መሆኑን ጠቁማለች።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: