#FastMereja I በሳምንቱ በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካች ያገኙ 10 የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ዝርዝር ይፋ ሲሆን፣ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ሙሉ በሙሉ በመያዝ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
የሙዚቃ መረጃዎችን ተንትኖ ደረጃ የሚያወጣው “የኔ ቫይብ” (YeneVibe) ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ሳምንታዊ መረጃ መሰረት፣ የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ስራዎች በሳምንቱ ውስጥ ብቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት የገበታውን አናት ተቆጣጥረውታል። ይህ ደረጃ የወጣው ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ አውቶማቲክ አሰራር ሲሆን፣ መለኪያውም ሙዚቃዎቹ በሳምንቱ ውስጥ በዩቲዩብ ላይ የጨመሩት የተመልካች ብዛት (New Views) ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
በደረጃው መሰረት “ዳስ ጣል (አንሳው)” የተሰኘው ስራ በሳምንት ውስጥ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በአጠቃላይ በሳምንቱ ምርጥ አስር ውስጥ የገቡት የቴዲ አፍሮ ስራዎች ብቻ መሆናቸው የአልበሙን ከፍተኛ ተቀባይነት የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የዲጂታል ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
በሳምንቱ ከፍተኛ ተመልካች ያገኙ ምርጥ 10 ሙዚቃዎች ዝርዝር፦
1ኛ ዳስ ጣል (አንሳው) – ቴዲ አፍሮ (+2,846,156 አዲስ እይታ)
2ኛ ሺ ቢባል (ወደ 90ዎቹ) – ቴዲ አፍሮ (+2,269,028 አዲስ እይታ)
3ኛ ዝ ፀዳል – ቴዲ አፍሮ (+1,933,851 አዲስ እይታ)
4ኛ ስምምነን (ጉሬጌ) – ቴዲ አፍሮ (+1,790,725 አዲስ እይታ)
5ኛ መርከብ – ቴዲ አፍሮ (+1,282,541 አዲስ እይታ)
6ኛ ታየኝ – ቴዲ አፍሮ (+1,278,335 አዲስ እይታ)
7ኛ ጽዮን ሙሽራዬ – ቴዲ አፍሮ (+1,171,738 አዲስ እይታ)
8ኛ ብልጭታ – ቴዲ አፍሮ (+1,126,840 አዲስ እይታ)
9ኛ ተወዳጅ – ቴዲ አፍሮ (+851,045 አዲስ እይታ)
10ኛ ጀምበር – ቴዲ አፍሮ (+755,029 አዲስ እይታ)
Source: FastMereja








No comments yet.