ኢራን በዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ገለጸች።

- Advertisement -
Sidebar AD

ኢራን በትልቁ የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ፍላጎቷን ስትገልጽ የውድድሩ አስተናጋጆች ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲቀበሉ ጠይቃለች።
የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ቅዳሜ እንዳስታወቀው በ2026 የክረምት ወቅት በሚካሄደው የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የሀገሪቱ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ይሳተፋል። ነገር ግን የጋራ አስተናጋጆቹ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ሁኔታዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ጋር እንዲያስማሙ ጠይቋል።

የኢራን ጥያቄ የተሰማው ካናዳ ባለፈው ወር ከፊፋ ጉባኤ በፊት የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሀላፊ ወደ ወደ ጉባኤው እንዳይገቡ መከልከሏን ተከትሎ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በጎርጎሪያኑ 2024 እንደ ሽብርተኛ ቡድን ከተፈረጀው የኢራን ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለም ክንድ ከሆነው ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ (IRGC) ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ነበር።
“በእርግጠኝነት በ2026 የዓለም ዋንጫ እንሳተፋለን፣ ነገር ግን አስተናጋጆቹ ስጋቶቻችንን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው” ሲል የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል።

ቅድመ ሁኔታዎቹ ቪዛ መስጠት እና ለብሔራዊ ቡድኑ ሰራተኞች አክብሮት መስጠት፣ የቡድኑ ባንዲራ እና ብሔራዊ መዝሙሩ በውድድሩ ወቅት እንዲሁም በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች እና ወደሚጫወቱባቸው ስታዲየሞች በሚወስዱ መንገዶች ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግላቸው መጠየቅን ያካትታሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የኢራን የእግር ኳስ ተጫዋቾች በውድድሩ ላይ መገኘታቸው መልካም መሆኑን ተናግረዋል።ነገር ግን አሜሪካ ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኢራን ልዑካን ቡድን አባላትን እንደ ሽብርተኛ ድርጅትነት ቆጥሮ ፈቃድ ሊከለክል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

የኢራን የእግር ኳስ ኃላፊ ታጅ ግን «ሁሉም ተጫዋቾች እና የቴክኒክ ሰራተኞች፣ በተለይም እንደ መህዲ ታሬሚ እና ኢህሳን ሃጅሳፊ ያሉ በእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን ወይም በIRGC ውስጥ ወታደራዊ አ አገልግሎት የሰጡ ያለምንም ችግር ቪዛ ሊሰጣቸው ይገባል» ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።
የዓለማቀፉ የእግር ኳስ ማሕበር ፊፋ ዋና ኃላፊ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በበኩላቸው ኢራን በታቀደው መሰረት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን ዩናይትድ ስቴትስ እንደምታደርግ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

DW Amharic


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1