የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችን ሹመት አጸደቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ባካሄደው 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጨምሮ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት በይፋ አፅድቋል፡፡

በዚህም መሰረት አቶ በላይ ደጀን የምክር ቤቱ የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ተቋማዊ አቅም ለማሳደግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ታስቦ የቀረቡት የሚከተሉት የቦርድ አባላት ሹመት ጸድቋል፡፡

1ኛ. አቶ ሞገስ ባልቻ – የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ ነቢዩ ባዬ – የሥራ አመራር ቦርድ አባል
3ኛ. አቶ ሠለሞን ካሳ – የሥራ አመራር ቦርድ አባል
4ኛ. ወይዘሮ ልዕልቲ ግደይ – የሥራ አመራር ቦርድ አባል
5ኛ. ዶክተር ሚኤሳ ኤሌማ – የሥራ አመራር ቦርድ አባል
6ኛ. ወይዘሮ ዘሃራ መሃመድ – የሥራ አመራር ቦርድ አባል

#አዲስአበባ #ሹመት #አዲስሚዲያኔትዎርክ #ምክርቤት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2