የዶክተር ፍቅሩ ማሩን ራዕይ የሚያስቀጥል ግዙፍ ሆስፒታል እየተገነባ ይገኛል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ዘርፍ ዘመናዊ አሠራርን በማስተዋወቅና የመጀመሪያውን የግል የልብ ሕክምና ማዕከል በመመሥረት ለሚታወቁት ለዶክተር ፍቅሩ ማሩ የዕውቅና እና የምስጋና መርሐ-ግብርም ተካሄዷል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የታዝማ የልብ ደም ስርና ቀዶ ሕክምና ማዕከል፤የዶክተሩን ታላቅ ራዕይ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ዘመናዊና ግዙፍ ሆስፒታል በመገንባት ላይ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

የታዝማ የልብ ደም ስርና ቀዶ ሕክምና ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው አለማየሁ፣ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከ16 ዓመታት በፊት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት “ታዝማ” የተሰኘውን የመጀመሪያውን የግል የልብ ሕክምና ማዕከል በመመሥረት በሀገሪቱ የሕክምና ዘርፍ የማይቻለውን አስችለዋል ብለዋል።

ዶክተሩ ሕክምና ከመስጠት ባለፈ፣ ለዘርፉ ዕድገት በርካታ የጤና ባለሙያዎች እንዲሰለጥኑና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና መጫወታቸውንም አስታውሰዋል።

ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት የዶክተር ፍቅሩን ራዕይ በስፋት ለማስቀጠል አዲስ ምዕራፍ ላይ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ በዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎች የተሟላ ግዙፍ ሆስፒታል በግንባታ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ይህ ሆስፒታል ተገንብቶ ሲጠናቀቅ፣ የልብ ቀዶ ሕክምናን ጨምሮ የተለያዩ ውስብስብ የሕክምና አገልግሎቶችን በጥራት፣ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕዝብ ተደራሽ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

ታዝማ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ በአዲስ አበባ፣ በጅማ፣ በጋምቤላ፣ በሀዋሳና በወለጋ በርካታ ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ አስቻለው፣ ይህ በጎ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ማዕከሉ ከጥቁር አንበሳና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች እንዲሁም ከሌሎች የመንግሥት የጤና ተቋማት ጋር በመተባበር ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

Photo:- Kebede Mekibeb

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: