ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ሄዋን ፋውንዴሽን አንድ ላይ ሆነው በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በደብረብርሃን መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ህፃናት ቤተሰቦች የቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ አስጀመሩ።
ዛሬ ግንቦት1/2018 ዓ.ም ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ሄዋን ፋውንዴሽን ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተጎጅዎች፣ ተፈናቃይ ህፃናት፣ ሴቶች፣ወጣቶች እና አረጋዊያን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ መልሶ ማቋቋም ስፖንሰርሺፕ ፕሮጀክት ማስጀመርያ ፕሮግራም አደረጉ።
በማስጀመርያ ፕሮግራሙ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ በድሉ ውብሸት፣ የደብረብርሃን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ መምርያ ኃላፊ ወ/ሮ በለጥሽ ግርማ፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ፣ የሄዋን ፋውንዴሽን ባለቤት ሄዋን ቀለመወርቅ፣ የሜሪ ጆይ ማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት አልባሳትን፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፣ የትምህርት መማሪያ ቦርሳዎችን እና ብስኩቶችን ለህፃናት ቤተሰቦች አጋርተዋል።
የሔዋን ፋውንዴሽን መሥራች ወይዘሮ ሔዋን ቀለመወርቅ እንዳሉት ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት የሁላችንም ድርሻ ነው ካሉ በኃላ የደብረ ብርሀን ህፃን ብቻውን አይሆንም እዚህ ከተማ ውስጥ ልጅ አይራብም ሲሉም ሀሣባቸውን ገልፀዋል።
የሚድያ ማስተባበር ሥራው በተወዳጅ ሚድያ የተከናወነ ነው።



Source: FastMereja









No comments yet.