ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ያላቸውን ግብ 70 በመቶ ማሳካታቸውን ገለጹ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን ላይ ካቀደቻቸው ግቦች መካከል 70 በመቶ ያህሉን ማሳካቷን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ እስካሁን በተከናወኑ እርምጃዎች የሚፈለገው ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አክለውም ፣ በቀጣይ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው የሚችሉ ሌሎች ተጨማሪ ኢላማዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል።
አሜሪካ ጥቅሟን ለማስከበርና የክልሉን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ እንደማትልም አፅንዖት ሰጥተዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት በከረረበት ወቅት የተሰማ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሁኔታውን በትኩረት እየተከታተለው ይገኛል ሲል አላራቢያ ዘግቧል።
ልዑል ወልዴ
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.