“ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት አልተቋጨም” ኔታንያሁ።።።።።።።።።።።።።።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ በኢራን…

- Advertisement -
Sidebar AD
“ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት አልተቋጨም” ኔታንያሁ
።።።።።።።።።።።።።።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ በኢራን ውስጥ የሚገኘው የበለጸገ ዩራኒየም ሙሉ በሙሉ እስካልተወገደ ድረስ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንደማያበቃ አስጠነቀቁ።
ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ያለው ውጥረት ገና መቋጫ እንዳላገኘና የቴህራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ዋነኛ ስጋት ሆኖ መቀጠሉንም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ከኢራን የሚሰነዘረው ጥቃትና ቀጠናዊ አለመረጋጋት አሁንም ባለበት በመሆኑ፣ እስራኤል ዝግጁነቷን እንደማታቆም ገልጸዋል።
ኔታንሁ ለሲ.ቢ.ኤስ «60 Minutes» ፕሮግራም በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ ምንም እንኳን በሀገራቱ መካከል የተኩስ አቁም ጥረት ቢኖርም፣ እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ስጋት እንደ ቀዳሚ አጀንዳ እንደምትይዝ  አስታውቀዋል።
ይህ መግለጫ የወጣው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ በከፍተኛ ደረጃ በጨመረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።
እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት እንደ ትልቅ ስጋት የምትመለከተው ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በቴህራን ላይ  ጫና እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች።
ዘ ናሽናል እና ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግበውታል
ቶማይ መኮንን
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: