የመጀመሪያው የሪል ስቴት የእግር ኳስ ውድድር ሊካሄድ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በአይነቱ ልዩ የሆነውና የሪል ስቴት ኩባንያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኘው “ኢትዮ ሪል ስቴት ካፕ” የእግር ኳስ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል። አርኪ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው ይህ ውድድር እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ የዘርፉን ተዋንያን ግንኙነት ለማጠናከርና የጠ/ሚ አብይ አህመድን የስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

​በዚሁ መሠረት በዕጣ ድልድል መርሃ ግብሩ መሰረት በምድብ “ሀ” ስር ጂ ፓወር፣ ዲኤምሲ እና ኢፎይ ለቤቴ የተደለደሉ ሲሆን፣ በምድብ “ለ” ደግሞ ቴምር፣ ሻምፒዮን ፕሮፐርቲ እና ጃምቦሮ ተመድበዋል። ቅዳሜ ዲኤምሲ ከጂ ፓወር በሚያደርጉት ጨዋታ ውድድሩ ይጀመራል።

​በውድድሩ ማጠቃለያ ላይ አንደኛ ለሚወጣው ቡድን የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት በተጨማሪ 300 ሺህ ብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሜዳልያ እና 200 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

የውድድሩን መጀመር አስመልክቶ በኦምና አዲስ ሆቴል በተከናወነው ይፋዊ መርሃ ግብር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዝርዝር መረጃዎች ተሰጥተዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: