የኦሮሚያ ክልል ለነገሌ አርሲ እግር ኳስ ክለብ የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ላደገው የነገሌ አርሲ እግር ኳስ ክለብ የ50 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ክለቡ በሊጉ እያሳየ የሚገኘውን ውጤታማ ጉዞ ለማጠናከርና ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ ይህንን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ መፍቀዳቸው ታውቋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ክለቡ የዞኑንና የክልሉን ስም በስፖርቱ ዓለም ለማስጠራት እያደረገ ላለው ጥረት እውቅና በመስጠት፣ ድጋፉ ለክለቡ ተጫዋቾችና አመራሮች ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: