ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ 15.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ
ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ውስጥ ባከናወናቸው መጠነ ሰፊ የኢንቨስትመንት እና የማስፋፊያ ሥራዎች ሳቢያ፣ ዓመታዊ ገቢው 15.9 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል።
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ130.9 በመቶ ዕድገት የታየበት መሆኑን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ ገልጸው፤ ኩባንያው በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን ሚና እያጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የሳፋሪኮም ንቁ ደንበኞች ቁጥር 13.6 ሚሊዮን መድረሱን ሰብሳቢው ጠቅሰው፤ ይህም የ54.2 በመቶ የደንበኞች ዕድገት ያሳየ መሆኑንና የዳታ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥርም 10.7 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸዋል።
ከኢንተርኔት ፍጆታ የሚገኘው ገቢ የኩባንያው የጀርባ አጥንት እየሆነ መምጣቱን አቶ ኤርሚያስ ጠቁመው፤ ከመደበኛው የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር፣ የኤም-ፔሳ (M-PESA) የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር በበጀት ዓመቱ ውስጥ በ119.4 በመቶ በመጨመር 5.2 ሚሊዮን መድረሱን አክለዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽነቱን ወደ 59 በመቶ በማሳደግ የደንበኞቹን የዲጂታል ተሞክሮ እያሻሻለ መሆኑን ሰብሳቢው አንስተው፤ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ 2.6 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ በሀገሪቱ በማፍሰስ፣ ለአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) የ1.5 በመቶ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.